ለጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች (ጥአመኢ) ወደተዘጋጀው ‹‹የዲጂታል ኢኮኖሚን ኃይል መጠቀም›› ወደሚለው ኦንላይን ትምህርት እንኳን በደህና መጡ! ይህ ትምህርት ተማሪዎች ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ እና ውጤታማ በሆነ መንገድ በኢ-ኮሜርስ ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚያስፈልጓቸውን ቁልፍ ብቃቶችን እና ክህሎቶችን እንዲጨብጡ ማስቻልን ዓላማው ያደረገ ነው።
ይህ ነጻ እና ለሁሉም ክፍት የሆነ የትምህርት ማስኬጃ ፕሮግራም ነው። በዚህ ትምህርት ውስጥ ያሉትን ጥቅሎች እና የትምህርት ይዘቶች በነጻ ሊያገኗቸው ይችላሉ። በዚህ ትምህርት ውስጥ ያሉትን ይዘቶች ደግመው የሚጠቀሟቸው ከሆነ፤ እባክዎ ምሉዕ እና ተገቢ የሆነ የባለቤትነት ማረጋገጫ ለሲአይፒኢ እና በእነዚህ ሞጁሎች ውስጥ የተካተቱት ይዘቶች ባለቤት ለሆኑ አካላት ይስጡ። ይህንን ትምህርት ለመውሰድ ሁለት አማራጮች አለዎት፡